የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምፅ አሰጣጡ ሂደት በሠላም መጠናቀቁን የሲዳማ ክልል ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ዋና አዛዥ ኮሚሽነር ተስፋዬ ዴቢሶ አስታውቁ።
በክልላችን በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ድምጽ የመስጠት ሂደት ፍጹም ሠላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የክልሉ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የተደራጀው የምርጫ ኮማንድ ፖስት በማደራጀት ወደ ሥራ መግባቱን ያስታወቁት የፖሊስ የጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ተስፋዬ ምንም አይነት ወንጀል አለመፈጸሙን ገልፀዋል።
ድምጽ የመስጠት ሂደቱ በስኬት እንዲጠናቀቅ ለጸጥታው ሥራ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን የመራጩ ህዝብ፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች፣ ዕጩዎች እና ታዛቢዎች ለሚዲያ ተቋማት ላበረከቱት አስተዋጽኦ እና ኃላፊነታቸውን በተገቢው ለተወጡ መላው የጸጥታ አካላትና ባለድርሻዎች ምስጋና አቅርበዋል።
በድህረ ምርጫ ያለው ሂደት በተመሳሳይ በስኬት እንዲከናወን ባለ ድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል ።
በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል !
Website
https://www.Sidamapolice.gov.et
Facebook :-https://www.facebook.com/share/1AK6
Telegram:-https://t.me/SIDAMAPOLICE
Whatsapp:_https://whatsapp.com/channel/0029VbBbBn9GpLHXYN9gJ537
TikTok :-https://www.tiktok.com/@sidamapolice4656
https://youtube.com/@sidamapoliceheadquarter...
የጠቅላይ መምሪያዉ በተጨማሪ ጥቆማ መቀበያ አድራሻዎች
046 220 9164
046 212 2468
የነፃ ስልክ 8295
P.B 511



