የሲዳማ ክልል ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ማኔጅመንትና የመምሪያ ኃላፊዎች የሜሪጆይ ኢትዮጲያ ሀዋሳ  የኩላሊት እጥበት ማዕከልን ጎበኙ።

የክልሉ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ተስፋዬ ዴቢሶ የሜሪጆይ ኢትዮጲያ ሀዋሳ የኩላሊት እጥበት ማዕከልን ተዘዋውረው በጎበኙበት ወቅት እንደገለፁት ማዕከሉ የኩላሊት እጥበት ለሚያስፈልጋቸው አካላት እያከናወነ ያለው በጎ ተግባር እጅግ ከፍተኛ መሆኑን ገልፀው ሀሉም የህብረተተሰብ ክፍል የማዕከሉን በጎ ተግባር በመደገፍ የበኩሉን እንዲወጣ ሲሉ አፅንኦት ሰጥተው አሳስበዋል።

የክልሉ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ከተቋሙ አመራርና አባላት ጋር በመወያየት ማዕከሉን የመደገፍ ስራ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

የሜሪጆይ ኢትዮጲያ መስራች ሲስተር ዘቢደር ዘውዴ ሀገር በቀል የሆነው ሜሪጆይ ኢትዮጲያ አረጋውያን ማዕከል በመላው ሀገሪቱ አረጋውያንን በመደገፍ ብዙ በጎ አድራጎት ስራዎችን እያከናወነ የሚገኝ ማዕከል ሲሆን በአሁኑ ወቅት በሀዋሳ ከተማ የኩላሊት እጥበት ማዕከልን ከፍቶ ለብዙ ችግርተኛ ወገኖች የኩላሊት እጥበትን በአነስተኛ ክፍያ እየሰጠ ይገኛል ብለዋል።

ኃላፊዋ አክለውም ማዕከሉ ባሰበው ልክ አገልግሎቱን ለማስቀጠል የፋይናንስና የማቴርያል ችግሮች ስላሉበት ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የበኩሉን እገዛ እንዲያደርግ ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

አመራሮቹም በአስተያየታቸው ፖሊስ ከህዝብ ወጥቶ ለህዝብ የሚያገለግል በመሆኑ አሁንም ከማዕከሉ ጎን በመሆን አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል።