የክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የክልሉን ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የበጀት አመቱን የለውጥ ስራዎችን ገመገመ።

በተቋሙ የተገኘው የገምጋሚዎች ቡድን የክልሉን ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የአገልግሎት አሰጣጥ፣ የስራ እቅዶችና አፈፃፀም እንዲሁም የመልካም  አስተዳደር  ችግሮች የተፈቱበት አግባብን በተመለከተ ምልከታ አድርገዋል።

በምልከታቸውም የክልሉ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የአገልግሎት አሰጣጥ መሻሻሎች ለህብረተሰቡ አፋጣኝ ፍትህን በመስጠት የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ እየተከናወነ ያለውን አበረታች ስራና ፈፃሚዎች ስራዎችን አቅደው ከመስራት አኳያ የተሻለ አፈፃፀም መኖሩ ተብራርቷል።
 
ተቋሙ በሁሉም የስራ ዘርፎችና በተቋማዊ ለውጥ የተሻለ  እንቅስቃሴ ውስጥ መሆኑን የገለፁት  የቼክ ሊስት ገምጋሚዎቹ ወደፊት ተቋሙ የምርጥ ተሞክሮ መቀመሪያ እንደሚሆን ገልፀዋል።