የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ተስፋዬ ዴቢሶ እንኳን ለ2019 ዓ.ም በሰላም አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል

የክልሉ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ተስፋዬ ዴቢሶ በመልዕክታቸው መላው የክልላችን ህዝብ፣መላው የፀጥታ አካላት ፣ውድ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያን በሀገር ውስጥና ከሀገር ወጭ ያላችው በሙሉ እንኳን ለአዲሱ ዓመት 2019 የዘመን መለወጫ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ብለዋል።

ኮሚሽነሩ አክለውም አዲሱ አመት የተቋማችን እራይ ግብ ለማድረስ የምንሰንቅበትና ለተግባራዊነቱ የምንተጋበት አመት መሆን እንዳለበት ገልፀዋል።

በመጨረሻም አዲሱ አመት ለሀገራችንና ለክልላችን ህዝቦች ፍጹም ሰላም የሰፈነበት፣ከወንጀል ስጋት ነፃ የሆነ ማህበረሰብ የሚፈጠርበት፣የሰላም፣የፍቅር የመተሳሰብ፣ የአብሮነት፣ የመቻቻል፣የዕድገትና የብልጽግና እንዲሆን መልካም ምኞት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።

በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል !